በርካታ ቁጥር ያላቸው ሞሮካውያን ፍልስጤምን በመደገፍ ሰልፍ አደረጉ

Date:

በሞሮኮ ዋና ከተማ በራባት በተደረገው ሰልፍ ላይ እስራኤል በጋዛ የምትፈፅመውን ጥቃት እንድታቆም ተጠይቋል።በሞሮኮ የሚንቀሳቀሰው ፍትህና እድገት ፓርቲ ፍልስጤማውያንን የሚደግፍ ለወራት የሚዘልቅ ግዙፍ ሰልፍ የጠራ ሲሆን ይህን ተከትሎም በአስር ሺዎች የሚቅጠሩ ሰልፈኞች ከበሮ እየመቱና ፍሊስጤማውያንን የሚደግፍ መፈክሮችን እያሰሙ በመሀመድ አራተኛ ጎዳና ላይ ሰልፍ አድርገዋል።

ሰልፈኞቹ የፍልስጤምን ባንዲራ ጨምሮ በእስራኤል የተገደለው የሀማሱ የፖለቲካ ሊቅ የያህያ ሲንዋርን ፎቶ ይዘው ታይተዋል። በሰልፉ ላይ ታዳጊዎች የተሳተፉ ሲሆን በጋዛ እየፈፀሙ ባሉ ጥቃቶች ለተገደሉት ህፃናት ማስታወሻነት የሚውል መሀሉ ላይ ቀይ ምልክት ያረፈበት ነጭ ባንዲራም ይዘው ተስተውለዋል።

በአሁኑ ሰዓት በጋዛ ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺ የተሻገረ መሆኑን የጋዛ ጤና ሚኒስተር ያስታወቀ ሲሆን በሰልፉ ላይም ነፃነት የፈለገን ሰው መገደል የለበትም የሚል መፈክር ጎልቶ ተሰምቷል።ሰልፈኞቹ እኛ ነፃ ፍሊስጤምን እንፈልጋለንም ያሉ ሲሆን “በወንጀለኛው ኔታንያሁ በጋዛ ላይ የተጣለው ከበባ መቆም አለበት በአፋጣኝ የነፍስ አድን እርዳታ ወደ ጋዛ መግባት አለበት” ሲሉም ተደምጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሰልፈኞቹ በአሜሪካ አመቻችነት እኤአ 2020 ዳግም የጀመረው የሞሮኮና የእስራኤል ግንኙነትም እንዲቋረጥ ጠይቀዋል።
@ዳጉ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...