በትግራይ ክልል 1.2 ሚሊየን ልጆች ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም

Date:

በትግራይ ክልል 1.2 ሚልዮን ሕፃናት እና አዳጊ ልጆች ወደ ትምህርት ገበታ አለመመለሳቸው ተገለጸ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ እንደገለጸው በትግራይ ከጦርነቱ በኋላ ጭምር የቀጠለው ሰብአዊ፣ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ሚልዮኖች ከትምህርት ገበታ እንዲርቁ አድርጓል።

በዚህም ላይ እስካሁን መፍትሔ ያላገኘው የተፈናቃዮች ጉዳይ ሌላው ልጆች ትምህርት ቤት እንዳይ ሄዱ እንቅፋት እንደሆነም ተገልጿል።

በዚህ ዓመት በትግራይ ክልል 2.5 ሚልዮን ተማሪዎች ነበሩ ወደ ትምህርት ቤት ይገባሉ ተብሎ የታሰበው፤ ሆኖም አሁን በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙት 1.3 ሚልዮን ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን የትግራይ ትምህርት ቢሮ ሐላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዑሽ ተናግረዋል።

ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ተማሪዎች ቁጥር ከመቀነሱ ጎን ለጎን የትምህርት ጥራቱ ላይም ክፍተት እየተስተዋለ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...

አሜሪካ እና እስራኤል ደቡብ ሊባኖስን ለአገሪቱ ጦር የማስረከብ ዕቅድ

አሜሪካ ድጋፏን በሰጠችው ዕቅድ መሠረት እስራኤል እና ሊባኖስ፤ የደቡብ...

የመሬት ልማትና አስተዳደር በበጀት ዓመቱ 63 በመቶ ያህሉን ማሳካት አልቻለም

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሊገባደድ በተቃረበው በጀት ዓመት ለመሰብሰብ...