ከታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ጋር የተገናኙ ወንጀሎች

Date:

የታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008

  1. ማንኛውም ሰው

ሀ. ከአንድ በላይ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የወሰደ ወይም ለመውሰድ የሞከረ እንደሆነ፤

ለ. የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን ሌላ ሰው እንዲጠቀምበት የሰጠ፣ ወይም

ሐ. የሌላን ሰው የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የተጠቀመ እንደሆነ፣ብር 20ሺ የገንዘብ
ቅጣት እና ከአንድ ዓመት እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ይቀጣል፡፡

  1. ከአንድ በላይ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የወሰደ ወይም ለመውሰድ የሞከረ እንደሆነ ታክስ ከፋዩ ለወሰደው ወይም ለመውሰድ ለሞከረው ለእያንዳንዱ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር በተናጠል ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
  2. የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ጥቅም ላይ የዋለው በዚህ አዋጅ አንቀጽ 14/6 የታክስ መለያ ቁጥር ባለቤት ለታክስ ወኪሉ መጠቀም እንዲችል በፅሁፍ ሲፈቀድለት እና የታክስ ወኪሉ የታክስ መለያ ቁጥሩን ለባለቤቱ ታክስ ጉዳዮች ብቻ ሲጠቀምበት የዚህ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ 1/ለ/ እና /ሐ/ ተፈፃሚ አይሆኑም፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...