ለትንሳኤ በዓል 5 ሺሕ 756 እንስሳት እርድ መፈፀሙን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታወቀ

Date:

ባሳለፍነው እሁድ ሚያዝያ 12 ቀን 2017 በተከበረው የትንሳኤ በዓል ላይ ወደ 6 ሺሕ 500 እንስሳት ይታረዳሉ ተብሎ በእቅድ ተይዞ የነበረ ሲሆን፤ 5 ሺሕ 756 እንስሳት እንዲታረዱ ማድረጉን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታውቋልል

በዚህም ድርጅቱ የእቅዱን 86 ነጥብ 6 በመቶ ማከናወን መቻሉን የድርጅቱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አታክልቲ ገብረሚካኤል ተናግረዋል።

ከእነዚህም ውስጥ 3 ሺ 200 የሚሆኑት የከብት ዘሮች ትላልቅ እንስሳት ሲሆኑ፤ እንደ በግና ፍየል አይነቶች ትናንሽ እንስሳት ደግሞ 2 ሺ 547 መሆናቸውን ገልጸዋል።

5 ሺ 756ቱም እንስሳት በዋናው የእንስሳት ማረጃ ቦታ “ቄራ” እና አቃቂ ቅርንጫፍ በሚገኘው በኩል በሁለቱም ቦታዎች እንዲታረዱ መደረጉንም አስታውቀዋል።

በድርጅቱ ሱቆች በኩል የሚደረጉ ግብይቶችን በተመለከተም ተመጣጣኝና የአገልግሎት ክፍያ ብቻ እንደሚያስከፍሉ አንስተዋል።

ለአብነትም አንድ በሬ ተመርምሮ፣ ታርዶ እና ታጥቦ ሲያበቃ ወደ ተጠቃሚው ለማድረስ 1 ሺሕ 457 ብር እንደሚያስከፍሉ ተናግረዋል።

በተደረገው ዝግጅት መሰረትም ምንም አይነት ችግር ሳይኖር ያለቅሬታ መስተናገዱን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አክለዋል።

“በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የታረዱ እንስሳትን ተረፈ ሥጋ ወደ ተረፈ ምርት የመቀየር ሥራ በጥሩ ሁኔታ ተከናውኗል” ሲሉም ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...