ሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ የሚገኘውና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የፈሰሰበት የመሮጫ መም እየተበላሸ መሆኑ ተገለጸ

Date:

ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ በሞጆ ደረቅ ወደብ አንድ ዓመት ከአራት ወራት መቆየቱ የሚነገርለት የመሮጫ መም (ትራክ)፣ በጊዜው ለታለመለት ጥቅም ባለመዋሉ ምክንያት በቆይታ ብዛት እየተበላሸ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ለአዲስ አበባ ስታዲየም ተብሎ የተገዛው ይህ የመሮጫ መም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ለሚፈለገው አገልግሎት እንዳይውል ምክንያት ተብሎ እየተጠቀሰ የሚገኘው የስታዲየሙ የሳር ተከላ ሥራ በታቀደለት ጊዜና ወቅት ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ ነው፡፡
አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲየም ከአራት ዓመታት በፊት የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ‹‹ዝቅተኛውን መሥፈርት አያሟልም›› በሚል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች ማናቸውንም አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን እንዳያስተናግድ ማገዱ ይታወሳል፡፡ መንግሥት የደረጃ ማሻሻያ ግንባታው የዓለም አቀዱ የዕገዳ ውሳኔ ዕውን በሆነ ማግሥት ቢጀምረውም፣ እስካሁን ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ ስታዲየሙ ከአገልግሎት ውጪ እንደሆነ ይገኛል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...