ናሚቢያ ትምህርት በነፃ እንዲሰጥ ተወሰነ !

Date:

የሀገሪቱ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ኔቱምቦ ናንዲ  ከ2026 በሃገሪቱ ባሉ በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ተቋማት  ዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ትምህር በነፃ እንዲሰጥ ተወሰነ ።

ፕሬዘዳንቷ ሀሙስ ማምሻውን ባደረጉት ንግግር ሀገሪቱ የሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክ ኮሌጆች “ምንም የምዝገባ [ወይም] የትምህርት ክፍያ አይከፍሉም ለተማሪዎቹም የምግብና መሰረታዊ ወጭዎች በመንግሥት ይሸፈናል ።አቅም ለሌላቸዉም   ድጎማ እና  የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ።

አክለዉም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በሁሉም የሀገሪቱ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ነፃ በሚሰጥባት ናሚቢያ ለትምህርቱ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ከቀጣይ አመት ጀምሮ  የሀገሪቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በነፃ ለማስተማር መንግስታቸው ከፍተኛ በጀት መመደቡን ገልፀዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነዉ ።

የ72 ዓመቷ ናንዲ-ንዳይትዋህ ከተመረጡ በኋላ በአንፃራዊነት ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ያለች ሲሆን በዋነኛነት በነዳጅ፣ በጋዝ እና በአረንጓዴ ሃይድሮጅን ዘርሮች ትክረት አድርገው በመስራት
ከፍተኛ የስራ አጥነት መጠንን በመቅረፍ በግብርናው ዘርፍ ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ እና በሀብት ላይ ያተኮረ ኢኮኖሚ በመገንባት ለዉጥ ማምጣታቸውን ይነገራል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...

እስራኤል በ40 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የመራጮች ተሳትፎ የታየበት ምርጫ አካሄደች

እስራኤል በ40 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የመራጮች ተሳትፎ የታየበት ምርጫ አካሄደ *...

አርሰናል ከካራባኦ ካፕ ውጪ ሆነ !

አርሰናል በሊግ ሁለቱ ክለብ ፍሌትውድ ታውን በመለያ ምት 5ለ3...