የገቢዎች ሃላፊ በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ

Date:

የመኪናው አንዱ የፊት ጎማ ከነቸርኬው ወልቆበት ፊት ለፊት ይጓዝ ከነበረ ሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው ” – የኦሮሚያ ክልል ትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ዋና መምሪያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከድር ፤ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ  ከሞጆ ወደ ባቱ ይጓዙበት የነበረው ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ ባጋጠመው የግጭት አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

ቃላቸውን ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጡት የኦሮሚያ ክልል ትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር  በላቸው ቲኪ ፥ በፈጣን መንገድ ከሞጆ ወደ ባቱ ይጓዝ የነበረ ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ ከሲኖ ጋር በመጋጨቱ የአንድ ሰው ህይወት ወዲያው ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

አደጋው የደረሰው ከቀኑ 9፡20 ሲሆን ኮድ3-75541 ኢት ላንድክሩዘር መኪና  አንዱ የፊት ጎማ ከነቸርኬው ወልቆበት ፊት ለፊት ይጓዝ ከነበረ ሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

በወቅቱ ምንም ዓይነት ግጭት ሳይኖር የፊት ጎማው የወለቀበት ምክንያት እየተጣራ መሆኑን ለቴሌቪዥን ጣቢያው አመልክተዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ፥ በአቶ አሊ ከድር ድንገተኛ ህልፈተ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው ፤ ትናንት በጽህፈት ቤታቸው ከተካሄደ የአመራሮች ስብስባ ወደ ስራ ሲመለሱ አደጋው እንዳጋጠመ ጠቁመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አይበገሬው ፍቃዱ —-  ( ከጋዜጠኛ ሁሴን ከድር )

ትናንት ( ቅዳሜ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም ) የቀድሞ...

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...