ኢትዮጵያዊቷ ማክዳ ሁሴን በአሜሪካ ትልቁን አለም አቀፍ የስነ-ፅሁፍ ውድድር አሸነፈች

Date:

ነዋሪነቷን በአሜሪካን ሃገር ያደረገችውና በኦቲዝም ላይ ከፍተኛ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት የምትታወቀው ማክዳ ሁሴን በሃገረ አሜሪካ የተካሄደውን አለም አቀፍ የስነ-ፅሁፍ ሽልማት ተሸላሚ ሆናለች።
በAUTHORS READING በተዘጋጀው ስምንተኛው አለም አቀፍ የሰነ-ፅሁፍ ውድድር ላይ በማክዳ ሁሴን አርሺ የተፃፈው “THE WORLD NEEDS A UNIQUELY HAPPY YOU” መፅሃፍ የሽልማቱ አንድ ዘርፍ በሆነው “Children’s book concept“ ዘርፍ የPENCRAFT BOOKS AWARD ተሸላሚ ሆናለች። በዚህ ውድድር ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ተወዳዳሪዎችም ተሳታፊ ነበሩ።

ይህ ማክዳ ተሸላሚ የሆነችበት Pencraft book award በ2009 እ.ኤ.አ በደራሲያን በተመሰረተው “AUTHORS READING” የሚሰጥ ሽልማት ነው።

መፅሐፉ ከድርጅቱ ኤዲቶሪያል ዳይሬክተር ከሆኑትና ከ1990 እ.ኤ.አ ጀምሮ በስነ ፅሁፉ አለም በቆዩት ዴቢድ ሄርን ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል።
ደራሲ ማክዳ አርሺ “Shining As I am” በሚል በእንግሊዝኛ ግጥም ተፅፎ በታገል ሰይፉ ወደ አማረኛ የተተረጎመው “እንዳለሁ አበራለሁ” የተሰኘና ለልጆች ኦቲዝም ምን እንደሆነ በቀላል ቋንቋ የሚያስረዳ እና በአንድ የኦቲዝም ተጠቂ ልጅ ላይ የሚያጠነጥን ታሪክ የያዘ መፅሃፍን ለንባብ አብቅታለች።
በተጨማሪም “የአለም መብራቶች” የተሰኘ የልጆች መፅሃፍን በእንግሊዘኛም በአማርኛም ፅፋ በአማዞን ላይ እየተሸጠ ይገኛል።

~ Yehualashet Zerihun

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...