55 ሺህ ነጋዴዎች በቁርጥ ግብር ሲከፍሉ መቆየታቸው ተገለጸ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የደረጃ “ሀ” እና  ደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች ውስጥ  55ሺህ የሚሆኑት  ነገዴዎች በቁርጥ ግብር ሲስተናገዱ እንደነበር  ተገለፀ ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ካሉ የሂሳብ መዝገብ እንዲዙ ከሚገደዱ  ከ1 መቶ 1 3 ሺህ በለይ  የደረጃ “ሀ” እና  ደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች ውስጥ  55ሺህ የሚሆኑት  ነጋዴዎች በቁርጥ ግብር ሲስተናገዱ እንደነበር  የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገልጷል ፡፡

ግብር ከፋዩ በህጉ መሰረት የሂሳብ መዝገብ ከመያዝ ይልቅ  በተለያዩ ምክንያቶች በቁርጥ ግብር ለመስተናገድ ካለው ፍላጎት እንደሆነ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነነት ዋና ዳይሪክተር አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል፡፡

የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ በህግ የሚገደዱ ግብር ከፋዮች ከመጪው ሀምሌ 1 ቀን  የግብር ማሳወቂያ ወር ጀምሮ ግን የተሟላ የሂሳብ መዝገብ በመያዝ ካልመጡ በስተቀር አይስተናገዱም  ሲል  አቶ ሰውነት   አስታውቀዋል፡፡

የሚዘጋጀው የሂሳብ መዝገብ ደግሞ ሙያዊ አውቀት ባለው ባለሙያ መዘጋጀት አለበት ያሉት ዋና ዳይሪክተሩ ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ ለማዘጋጀት  የሚያስችል ዝግጂት ከወዲሁ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል:

ኢትዮ ኤፍ ኤም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች”:-  ከዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል ጋራ ውይይት

ዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል በተለይ በ1997 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ 97...

የ12ኛ ክፍል የፈተና ቀን ታወቀ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሳልቫ ኬር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት...

አሜሪካ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ልታነሳ ነው !

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ያላትን ግንኙነት...