አፍሪካ ውስጥ ሁለት ጂኦ ፓርኮች ብቻ መመዝገባቸው “አሳዛኝ” ነው

Date:

ይህንን እውነታ ለመቀየር ያሰበ ቀጣናዊ መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፍቷል። የቱሪዝም ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ጋር በመተባበር ያሰናዳው ዝግጅት በዘርፉ ኢትዮጵያ የያዘችውን አቅም አጉለቶ ለማሳየት ያለመ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ጂኦ ፓርኮችን ማስመዝገቧ ለምርምር እንደሚጠቅም፣ በዙሪያቸው ያሉ ማሕበረሰቦችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ እና ዓለም አቀፍ እውቅናን እንዲያገኙ እድል እንደሚፈጥር የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ ጂኦ ፓርኮች ቁጥር 229 እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በጂኦ ፓርክነት ልታስመዘግባቸው የሚችሉ ብዙ ቦታዎች እንዳሏት የጠቆሙም ሲሆን ለማሳያነት በጠቀሱት መልካ ቁንጥሬ የመድረኩ ተሳታፊዎች ምልከታ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

መልካ ቁንጥሬ መካነ ቅርስን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ለዩኔስኮ ሠነድ መላኩ የሚታወስ ነው፡፡ ቦታው የሰው ልጅ፣ የእንስሳትና የጥንት የሰው ልጅ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የድንጋይ መሳሪያዎች እንደሚገኙበት ይነገራል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...