በሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ በተፈፀመ የመድፍ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎችም ቆስለዋል ተብሏል።
ትናንት መገባደጃ ላይ የጀመረው የፈጥኖ ደራሹ ጥቃት በመኖሪያ ሰፈሮች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ሁለት ሴቶችን እና ህጻናትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ ቢያንስ 15 ሌሎች ወደ ሆስፒታሎች ተወስደዋል።
ሰራዊቱ በተጨማሪም፤ በከተማው የፈጥኖ ደራሹ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎችን መግደሉን ተናግሯል።
ለአምስቱ የዳርፉር ግዛቶች ቁልፍ የሰብአዊነት ማዕከል በሆነችው ከተማ ውስጥ ስላለው ሁከት ዓለም አቀፍ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም፤ ኤል-ፋሸር ከግንቦት 2024 ጀምሮ በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሹ ሃይል መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደባት ይገኛል፡፡
የተባበሩት መንግስታት እና የሀገር ውስጥ አኃዛዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል 15 ሚሊዮን ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡
በአሜሪካ መሰረታቸዉን ያደረጉ ተመራማሪዎች ደግሞ የሟቾች ቁጥር እስከ 1መቶ 30 ሺህ ይደርሳል ብለው ይገምታሉ።
