የዓለማችን ድሃው ፕሬዝዳንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

Date:

ፔፔ በመባል የሚታወቁት የቀድሞ የኡራጓይ ፕሬዝዳንት ሆሴ ሙጂካ በ89 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። እ.ኤ.አ. ከ2010 እስከ 2015 ኡራጓይን ያስተዳደሩት የቀድሞ ሽምቅ ተዋጊ “የዓለማችን ድሃው ፕሬዝዳንት” ተብለው የሚታወቁት በመጠነኛ አኗኗራቸው የተነሳ ነበር። የወቅቱ የኡራጓይ ፕሬዝደንት ያማንዱ ኦርሲ የፔፔን ህልፈት በተመለከተ በኤክስ ላይ ባጋሩት መልዕክት “ስለሰጠህን ነገር ሁሉ እና ለህዝብ ስለነበረር ጥልቅ ፍቅር እናመሰግናለን።” ብለዋል።

ፖለቲከኛው የሞቱበት ምክንያት በውል ባይታወቅም በካንሰር ሲሰቃዩ ቆይተዋል። በፕሬዚዳንቱ ለመኖር የመሩጡበት ቀላል መንገድ ምክንያት እንዲሁም ኡራጓይ የማሪዋናን እፅ ለመዝናኛን ሕጋዊ በማድረግ የመጀመሪያዋ ሀገር እንድትሆን ያሳለፉት ፕሬዝዳንቱ በላቲን አሜሪካ እና በመላው ዓለም ታዋቂ የፖለቲካ ሰው ሆነው ዘልቀዋል።ሰዎች የዓለማችን ድሃው ፕሬዝዳንት ብለው ይጠሩኛል እኔ ግን ድሃ እንድሆንኩ አይሰማኝም ድሃዎች የተቀናጣ ህይወት ለመኖር የሚያግበሰብሱ ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት ይኖሩበት ከነበረ የገጠር መኖሪያ ቤታቸው ከስልጣን ሲወርዱ መኖር የጀመሩ ሲሆን መኪናቸውም የ1987 ስሪት የሆነውን ቮልስ ቫገን እና በስማቸው ተመዝግቦ የሚገኝ ስልሳ ዓመታት ያገለገለ ሳይክል አላቸው። 90 በመቶ ደሞዛቸውን ለበጎ ኡድራጎት እንዲውል ማድረጋቸውም ይታወሳል። ባለፈው ዓመት በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ሞት የማይቀር ነው፤ ምናልባት የህይወት ጨው ሊሆን ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል። በሙስናም ሆነ በዲሞክራሲ ጥሰት ክስ ካልቀረበባቸው ጥቂት መሪዎች መካከል ቀዳሚው ናቸው።

#ዳጉ_ጆርናል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...