የግብርና ሚኒስቴር የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶች በእንስሳት እርባታ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያስችል የኢትዮጵያ የእንስሳትና ዓሳ ኢንቨስትመንት ሰነድ ይፋ አድርጓል።
ይህ ሰነድ መንግስት ባለፉት ስድስት ዓመታት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ከመሆኑ ባሻገር የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ የሃገሪቱን የእንስሳት ሃብት አቅም ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ያለመ ነው ተብሏል።
በሰነዱ ዝግጅት ላይ የዘርፉ ተመራማሪዎችና ባለድርሻ አካላት እንደተሳተፉ የግብርና ግብዓትና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሶፊያ ካሳ ገልጸዋል። ሰነዱም በሃገሪቱ ያለውን የእንስሳት ሃብት እምቅ አቅምና እስካሁን በአግባቡ ጥቅም ላይ አለመዋሉን ያሳያል። ከዚህም በተጨማሪ ወደ ዘርፉ ለመግባት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች አስፈላጊ መረጃዎችን እንዳካተተ ተገልጿል።
