የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሰባት አባላት ያሉትየአጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ አባላትን ሠየመ

Date:

ለ፳፻፲፯ ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህንት ጉባኤ አጀንዳ በማርቀቅ እንዲያቀርቡ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን የሰየመ ሲሆን  ኮሚቴው በቋሚ ሲኖዶስ ተዘጋጅቶ የቀረበውን አጀንዳ በመመርመርና በማሻሻል ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በማቅረብ የሚያጸድቅ ይሆናል። የኮሚቴው አባላትም፦

፩.አቡነ ጎርጎርጎሬዎስ
፪.አቡነ ቀሌምንጦስ
፫.አቡነ ኤልያስ (አርባ ምንጭ)
፬.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ
፭.አቡነ ሩፋኤል
፮.አቡነ ዜናማርቆስ
፯.አቡነ ኤልሳዕ ሲሆኑ ምልዓተ ጉባኤው  ከአጀንዳዎቹ መጽደቅ በኋላ  የቅዱስ ፓትርያርኩን የመግቢያ መልዕክትና የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤትን ሪፖርት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
  ሐዋርያት ፳፥፳፰

🔵የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...