የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ለህይወትና
ለንብረት ስጋት በሆኑ 242 ሺህ 179 ጨለማ የሚበረታባቸው ቦታዎች መብራት ማስገባቱን አስታውቋል።
አካባቢዎቹ ድቅድቅ ጨለማ የነበሩ በመሆናቸው ለዝርፊያ፣ ጉዳት ለማድረስናሕይወትን ለማጥፋት ምቹ እንደነበሩ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ ገብሬ ዳኘው ለአራዳ ገልጸዋል።
ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ራሱን የቻለ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሲሰራ ቆይቷል ያሉት አማካሪው፥ መብራቶቹ መሰራታቸው የመፍትሄው አንድ አካል መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ወደ 72 ሺህ 378 በሚሆኑ ጨለማ ቦታዎች ላይ መብራት ለማስገባትዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል።
እንዲሁም ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት በሆኑ አራት ቦታዎች ላይ የፖሊስ ማዕከላት መሰራታቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም እንደነዚህ አይነት ስጋት ያለባቸውን ቦታዎች በመለየት ወንጀልንየመከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።
