ቼልሲ ማንቼስተር ዩናይትድን አሸነፈ

Date:

በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ማንቼስተር ዩናይትድን 1 ለ ዐ አሸንፏል።

የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ቼልሲ ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ማርክ ኩኩሬያ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል።

ቼልሲ የምሽቱን ድል ተከትሎ ነጥቡን 66 በማድረስ በኒውካስል ዩናይትድ በግብ ክፍያ ተበልጦ 4ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በውድድር አመቱ በፕሪሚየር ሊጉ ብቻ 18ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ቀደም ብሎ ምሽት 3:30 በተደረገው ጨዋታ አስቶን ቪላ ቶተንሃም ሆትስፐርን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ወሳኝ 3 ነጥብ አሳክቷል።

የአስቶንቪላን ግቦች ኮንሳ እና ካማራ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፈዋል።

ቪላ ነጥቡን 66 በማድረስ በኒውካስል ዩናይትድና ቼልሲ በግብ ክፍያ ተበልጦ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፥ ሽንፈት ያስተናገደው ቶተንሃም በነበረበት 17ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...