በየዓመቱ ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች በትምባሆ ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ

Date:

በኢትዮጵያ በየዓመቱ የትንባሆ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን አምስት በመቶ የሚሆኑ ሰዎች የትንባሆ ተጠቃሚዎች እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።በኢትዮጵያ በዓመት 16 ሺ 800 ሰዎች በትምባሆ ምክንያት ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተነግሯል።

በተለይ ወጣቶችና  የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ዜጎች ለችግሩ ያላቸው ተጋላጭነት የጎላ በመሆኑ ጤናማ ዜጋን ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ሲሉ  የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን  የምግብና የጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በትምባሆ እና በኒኮቲን ምርቶች ላይ የትምባሆ ኢንዱስትሪ ስልቶችና ጭምብሎችን ማጋለጥ” በሚል መሪ ቃል  የአዲስ አበባ ከተማ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን  ሜይ 31 የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን በማስመልከት  ከተማ አቀፍ የፀረ-ትምባሆ ንቅናቄ ከሚያዚያ 25  እስከ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ትምባሆ በየዓመቱ ከ8 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን እንደሚገድል እና ከነዚህ ውስጥ 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑት ሳያጨሱ የሚጨስባቸው ሰዎች እንደሚገኙበት ጥናቶች ይጠቁማሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...