የተቋማት ገለልተኝነት ባለመኖሩ ህገ መንግስቱ እንዲፈፀምና ሲጣስ ደግሞ እንዲጠበቅ የሚደረግበት ሁኔታ እንዳይኖር ማድረጉን አራዳ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ተናገሩ። ፓርቲዎቹ ህገ መንግስቱ መሻሻል ያለባቸው ህጎች እንዳሉት ሁሉ ዓለም አቀፍተቀባይነት ያላቸው ድንጋጌዎችንም መያዙን ገልፀዋል።
በህገ መንግስቱ የአፈፃፀም ችግር ምክንያት ሊፈቱ የሚችሉ ነገርግን ያልተፈቱ ችግሮች አሉ የሚሉት ፓርቲዎቹ ይህም የፌደሬሽን ምክርቤት ገለልተኛ አለመሆን ነው ብለዋል።
ህግ ያወጣው፣ የተረጎመውና የሚያስፈፅመው አካል ህጉን የሚጥስ ከሆነ የህገመንግስት የበላይነት አይኖርም ነው የተባለው።
ህገ መንግስቱ ይሻሻል የሚለው ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ህገ መንግስቱ ችግር ስላለበት ሳይሆን ለግጭት የሚዳርጉ ህጎች እንዲታዩ ነው የሚሉት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ለስራ ምቹ የሆኑ የህገ መንግስቱ ክፍሎች ግን ተፈፃሚእየሆኑ አይደለም ብለዋል።
