በደብረ ብርሃን ከካንፕ ውጪ ላሉ ተፈናቃዮች ከሦስት ወር በኃላ ድጋፍ ተደረገ

Date:

በደብረብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች የተቋረጠባቸዉ ድጋፍ ከወራት በኋላ ማግኘት መቻላቸዉን ገለጹ።

ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች በቂ ደጋፍ እየተደረገላቸው አለመሆኑን ሲያነሱ ቆይተዋል።

ከዚህ ቀደም ለሃገሬ ቴሌቭዥን በቦታው የሚገኙ ተፈናቃዮቹን በማናገር ዘገባዎች ወደ እናንተ አድርሶ ነበር ፡፡

ከተፈናቅሉ 5ኛ አመታቸዉ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ጣቢያችን ያናገራቸው አስተባባሪዎች የመንግስት አካል እስካሁን አነጋግሯቸው እንድማያዉቅ ገልጸዋል፡፡  

ተፈናቃዮቹ ከሶስት ወር በኃላ አሁን ላይ ድጋፍ እንደተደረገላቸዉ በመግለጽ ድጋፉን ላደረጉላቸዉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አሁንኑ ድጋፍ  ካለው ችግር አንጻር በቂ አለመሆኑንና በሁለትና በሶስት ወራት አንዴ የሚደረገዉ ድጋፍ በየወሩ እንዲደረግላቸዉና በቋሚነት የሚቋቋሙበት መንገድ እንዲያመቻችላቸዉ ጠይቀዋል፡፡

(ሀገሬ ቴቪ)፤

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...