የቀድሞው የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አለማየሁ ጢሞቲዮስ ያለመከሰስ መብት ተነሳ

Date:

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር ምርጫ 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የምክር ቤት አባሉን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

ግለሰቡ በስልጣን ያለ አግባብ መጠቀም፣ በሙስና፣ በቀጥታ በኮንትሮባንድ ዝውውር  ውስጥ መሳተፍ፣ ለኮንትሮባንድ አዟዟሪዎች በጥቅም ትሰስር ምቹ ሁኔታ መፍጠር እና  አደንዛዥ ዕጽ በማዘዋወር እንቅስቃሴ ውሰጥ መገኘቱን የክልሉ ፍትህ ቢሮ ለምክር ቤቱ በዝርዝር አቅርቧል።

የምክር ቤት አባላት በግለሰቡ ዙሪያ የቀረበውን ዝርዝር መረጃ ካደመጡ በኋላ፤ ሌሎች ከግለሰቡ ጋር በጥቅም ትስስር የወንጀል ተሳትፎ ያላቸው አካላት ላይ በጥልቀት ፍተሻ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል።

ግለሰቡ ስልጣኑን መከታ በማድረግ የፈፀማቸው ነገር ግን በወንጀል ሪፖርቱ ውስጥ ያልተካተቱ በርካታ ኢ-ፍትሀዊ ድርጊቶች መኖራቸውን በምክር ቤት አባላቱ ተነሰቷል።

ምክር ቤቱ የግለሰቡ ያለመከሰስ መብትን ለማንሳት የቀረበለትን አጀንዳ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

ምክር ቤቱ በሌላ በኩል የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ስያሜ “አፊኒ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን” እንዲሆን የቀረበለትን አዋጅ መርምሮ ውድቅ በማድረግ የሚዲያ ተቋሙ ቀድሞ ይጠራበት በነበረው ስያሜ “የሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን” ሆኖ እንዲቀጥል ውሳኔ  አሳልፏል።

በሚካኤል ገዙ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...