ሂጅራ ባንክ የወጣት ስራ ፈጣሪዎችን ”ሲራራ አዋርድ”በሚል የሽልማት መርሃ ግብር አካሄደ

Date:

የሽልማት ስነ ስርዓቱም  የመንግስት ሀላፊዎች፣ የባንኩ ሀላፊዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች በተገኙበት መካሄዱ ተሰምቷል።

በውድድሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡትም መሸለማቸውን ባንኩ የላከልን መግለጫ ያስረዳልዕ።

በአንደኛ ደረጃ  ያጠናቀቀው ስራ ፈጣሪ  ሚልኪያስ አህመድ(ዶ/ር ) ሲሆን ለአሸናፊነት ያበቃውም የአፈር ማዳበሪያ ከእንስሳት አጥንት ማግኘት በመቻሉ መሆኑ ተጠቅሷል።

በዚህ የስራ ፈጠራውም የ 3,000,000 የቀርደል ሀሰን ፋይናንስኪንግዕ (ከወለድ ነፃ ብድር) እና 300,000  ብር ተሸላሚ ሆኗል።

የሂጅራ ባንክ የሲራራ ስራ ፈጠራ ውድድርን በሁለተኝነት ያጠናቀቀው  ስራ ፈጣሪ  ደግሞ ዩሱፍ አሊ  ይባላል።

የፈጠረው ስራም የገበሬዎችን የዕለት ተዕለት አድካሚና ኋላቀር የአሰራር ዘዴዎችን ወደ ተሻሻለ ደረጃ ለማምጣት የሚያስችል የእህል ማጨጃ ማሽንን መሆኑን ሰምተናል።

ወጣቱ ለዚህ ፈጠራው የ1,000,000  ቀርደል ሀሰን ፋይናንሲንግ እና የ 200,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል።

እንዲሁም ሙሃመድ ጁሃር በትንሽ ኃይል የሚሰራ የዶሮ እንቁላል ማፈልፈያ ማሽን በመስራት የሶስተኛ ደረጃ አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቀ ሲሆን 500,000 የቀርድ ፋይናንሲንግ ሺልማት እና 100,000  ተሸላሚ መሆኑን ባንኩ ነግሮናል።

በተጨማሪም ጣሂር ኢሳ እና ኢሳቅ ጋሊ እንዲሁም ኢብራሂም አሊ በቅደም ተከተል 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል።

ንጋቱ ሙሉ ( ሸገር 102.1 )

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...