ለ472 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ!

Date:

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለ472 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ። የክልሉ መንግሥት ከፊታችን የሚከበረውን 1 ሺህ 446ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓል እና መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ472 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉ ተገልጿል።

በወንጀል ጉዳይ እስራት ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት ከሚገኙት ውስጥ ሕጉ የሚጠይቀውን መመዘኛ አሟልተው ለተገኙ በመደበኛ ለ459 ወንዶች እና ለ12 ሴቶች እንዲሁም በልዩ ሁኔታ ለ1 ሴት የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ስለመደረጉ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳደር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መናገራቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል፤ 471 በሙሉ ይቅርታ ከእስር እንዲለቀቁ መወሰኑም ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...