ለሰራተኞቹ የ 35 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግ ተስማሙ

Date:

ባለፈው ሐሙስ ከአሰሪው ድርጅት ጋር ባለመግባባታቸው ስራ ያቆሙት የዲኤችኤል/DHL ሰራተኞች ከዛ በኋላ በተደረገ ድርድር የሰራተኛ ማህበሩና ድርጅቱ ስምምነት በ35% ጭማሪ መስማማታቸውን ቲክቫህ አስነብቧል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ፅ/ቤት አሸማጋይነት የሰራተኛ ማህበሩ እና ድርጅቱ በ35% ጭማሪ ተስማምተዋል።የድርጅቱ ሰራተኞች በነገው ዕለት ማለትም ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ስራ እንደሚመለሱ ተነግሯል፡፡

ይኸው አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን በሰራተኛ ማህበሩ በኩል የተጠየቀ ቢሆንም ድርጅቱ ባለመስማማቱ፣ የ 35 ከመቶ ጭማሪው ከግንቦት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ነው የተገለፀው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...