በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚከናወነውን የኢፍጣር መርኃ ግብር ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር ጋር ተያይዞ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ።
በዚህም መሰረት፡-
- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን
- ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ
- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች አጎና ሲኒማ፤ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ
- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ
- ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ
- ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጧር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ ይደረጋሉ።
በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን አስተላልፏል።
