በዘርፉ ባለሞያዎች ለዚህ ችግር ምክንያት የተባሉ ነጥቦች ተዘርዝረው ሲቀርቡ ይሰማል፡፡
በትምህርት ዙሪያ የሚሰራ ተቋም አጠናሁት ብሎ ይፋ ባደረገው ውጤት የኢትዮጵያ የት/ት ሥርዓት ተማሪ የተሳሳተውን እንዲያውቅና መልሶ እንዲያርም እድል አለመስጠቱ ትልቁ ችግር ነው ብሏል፡፡
ተማሪዎች በፈተናዎች ወቅት የሚያገኙትን የተሳሳቱ መልሶቻቸውን እንዲያርሙ እድል አለመስጠታቸው እንደ ዋና ችግር ተመልክቼዋለሁ ያለው በዘርፉ ለ20 ዓመታት ሲሰራ የቆየው ዕርግብ የትምህርት አገልግሎት ይህም የስራ አጥ ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል፣ ተማሪዎች ከሌሎች የአለም ሀገራት ጋር ተወዳዳሪነታቸው ዝቅተኛ እንዲሆን እና ሌሎች ችግሮችን አስከትሎብናል ብሏል።
በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በአማካይ በዓመት ከ700 ሚሊዮን እስከ 1 ቢሊየን ኤክስ ለተማሪዎች እንደሚሰጥ ተመልክተናል ያሉት ዕርግብ የትምህርት አገልግሎት የእቅድ አስተዳደር ሀለፊ አቶ መርሃዊ ጎሹ አበበ አንድ አስተማሪም በዓመት እስከ 20,000 ኤክሶች ለተማሪዎች ይሰጣል ብለውናል፡፡
ለትምህርት ሥርዓቱ ዋነኛው ችግር ስህተትን አለማረም ሆኖ አግኝቸዋለሁ ያለው ድርጅቱ ይህ ችግር ደግሞ አሁን ላለንበት የትምህርት ምስቅልቅል ዳርጎናል ብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/63e-rtd/
ከሸገር 102.1
