በአዲስ አበባ ከተማ በመንገድ ዳር የሚገኙ የንግድ ወይም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከምሽት 12 እስከ ንጋት 12 ድረስ “የውጭ” እና “የውስጥ መብራት” ካላበሩ እንዲሁም በምሽት ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን የሚያሳይ በመብራት የሚሰራ ምልክት ካላስቀመጡ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት ሊያስቀጣቸው የሚችል ደንብ የከተማዋ አስተዳደር ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።
ደንቡ፣ በመንገድ ዳር የሚገኙ ማናቸውም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የንግድ መደብሮች እንዲሁም መኖሪያ ቤቶች በሕንጻቸው የፊተኛው ገጽ መብራት ወይም የፋሳድ ላይት መብራት የማስገባት ግዴታ ጥሎባቸዋል።
