ማንም ሰው አላምንም ማለት ይቻላል- ትራምፕ

Date:



‎ዶናልድ ትራምፕ ለቢቢሲ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ ከፑቲን ጋር የነበራቸዉ ልዩ የስልክ ለዉዉጥ ተስፋ ቢስ ቢሆንም ጉዳዩን ግን አልጨረስኩም ብለዋል፡፡

‎የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የሩሲያውን መሪ እንደሚያምኗቸዉ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽም፤ ማንም ሰው አላምንም ማለት ይቻላል ብለዋል፡፡

‎ትራምፕ ይህን የተናገሩት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ለመላክ ማቀዳቸውን ካስታወቁ ከሰዓታት በኋላ ሲሆን፤ በ50 ቀናት ውስጥ የእርቅ ስምምነት ካልተደረሰ በሩሲያ ላይ ከባድ ታሪፎች እንደሚጣሉ አስጠንቅቀዋል።

‎ትራምፕ በዩክሬን ጦርነትን ለማቆም ከሩሲያ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ለአራት ጊዜ ያህል አስበው እንደነበር ተናግረዋል።

‎ስለ ፑቲን ተጠይቀዉ በሰጡት ምላሽም ‹‹በእርሱ ተስፋ ብቆርጥም አልጨረስኩም፤ በእርሱ ግን ተስፋ ቆርጫለሁ›› ሲሉ መልሰዋል፡፡

‎‹‹ጥሩ ውይይት እናደርጋለን፤ ሂደቱም ጥሩ ነው ብዬ ሊሳካ እንደምንቃረብ ሳስብ እሱ በኪቭ አንድ ሕንፃ ያፈርሳል›› ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...