ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ “አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በዋናነት በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ቀውስ ለመቃወም፣ የአፈሳ ተግባራት እንዲቆሙ ለመጠየቅ እና ለፌደራል መንግስት እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድምፅን ለማሰማት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በዕለቱም ሰልፈኞቹ “የትግራይ እናቶች እንባ ይቁም” የሚሉና ልዩ ልዩ መልዕክቶችን ያዘሉ መፈክሮችን በማንገብ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የተካሄደው ይህ ሰልፍ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሲሆን፣ መልእክታቸውን በሰላማዊ መንገድ ማስተላለፋቸው ተገልጿል
