ስምንት ሺህ የልብ ህሙማን ታካሚዎች ህክምና ለማድረግ ወረፋ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተገለጸ

Date:

የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ማህበር በ2024 በጀት ዓመት ከ12 ሺህ በላይ የተመላላሽ የልብ ሕክምና ክትትል እና 669 ለሚጠጉ ታካሚዎች ደግሞ የህክምና አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል።

ለታካሚዎች የሰጠው አገልግሎት በገንዘብ ሲተመን ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የልብ ቀዶ ሕክምና እና በ ደም ስር በኩል የሚሰጥ  የህክምና አገልግሎት መሆኑን  በኢትዮጵያ  የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ  ማዕከል የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን  ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ዳዊት እሸቱ ተናግረዋል ።

ማዕከሉ ምንም እንኳን ነጻ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ቢሆንም አንድ ቀዶ ህክምና ለመስራት ተቋሙ የሚያወጣው  ወጪ ከ100 ሺህ ብር በላይ እንደሚሆን ተጠቁሟል። አንድ ታካሚ መጀመሪያ ከታየበት ቀን አንስቶ ቀዶ ህክምና እስከሚሰራበት  ቀን ድረስ ለዓመታት ወረፋ ሊጠብቅ  እንደሚችል ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በተያዘው በ2025 ዓመት   ከ17,000 በላይ ለሚሆኑ ታካሚዎች አገልግሎት  ለመስጠት እንዲሁም 352 የልብ ቀዶ ህክምና እና 334  በደም ስር በኩል የሚሰጥ ህክምና ለመስጠት በዕቅድ መያዙን ተጠቁሟል። በአሁን ሰዓት አጠቃላይ ታካሚዎች ቁጥር 20 ሺህ ሲሆን ወረፋ የሚጠብቁ ታካሚዎች ደግሞ ስምንት ሺህ መሆናቸውን አንስተዋል። ይሁን እና ተቋሙ ለህክምናው  የሚያስፈልጉ  እቃዎችን ለማሟላት ችግር እንደሆነባቸው ገልጸዋል። በተለይም መድሃኒቶች  በበቂ ሁኔታ አለመኖራቸው በታቀደው ልክ ህክምና  መስጠት  እንዳይቻል  ትልቅ ተግዳሮት መሆኑን ዶክተር ዳዊት እሸቱ ጨምረው ብሥራት ሬዲዮ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...