ኬንያ የተለበሱ ልብሶችን ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ቀዳሚዋ የአፍሪካ ሃገር ሆነች

Date:

ከዚህ በፊት የተለበሱ ልብሶችን (ቦንዳ) በብዛት የምታስገባዋ አፍሪካዊት ሃገር ናይጄሪያ የነበረች ሲሆን አሁን ይህንን ደረጃ ኬንያ መረከቧን ማሳቹሴትስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ አስታውቋል።

እንደ መረጃው ከሆነ ኬንያ በ2023 ብቻ 298 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸውን የተለበሱ ልብሶች ወደ ሃገር ውስጥ አስገብታለች።

ከኬንያ በመቀጠል ጋና፣ ደቡብ አፍሪካና ኡጋንዳ ብዙ የተለበሱ ልብሶችን ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ተቀምጠዋል።

ኬኒያዊያን በዚሁ ላይ የተሰማሩ ወደ 2 ሚሊዮን ነጋዴዎችን ድምጽ ያስተጋባል ያሉትን ማኅበርም አላቸው (Mitumba Consortium Association) በዚህ ማኅበራቸው ፖሊሲዎች እንዲሻሻሉ እና በዘርፉ ያሉ የተሳሳቱ የሚሏቸውን ምልከታዎች ይሞግቱበታል።

በሃገራችን ኢትዮጵያም እነዚህ ልብሶች 53 በመቶ የሚሆነውን የጨርቃ ጨርቅ ገበያ እንደያዙ መዘገቡ ይታወሳል።

የተለበሱ ልብሶች ንግድ ትልቅ ኢኮኖሚ የሚፈጥር እንደሆነ የሚከራከሩ ቢኖሩም በዚያው ልክ የቴክስታይሉን ዘርፍ ያቀጭጨዋል በሚል የሚሞግቱም አሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...