በሃዘን ለተጎዱ ቤተሰቦች እንድረስላቸው!

Date:

በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ አካባቢ በሚገኘው የኮየ ፈንታ ደብረ ፀሐይ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በበዓለ ጥምቀት ዕለት በአሳዛኝ የኤሌክትሪክ አደጋ አራት ወጣት አስተባባሪዎችን ማጣታችን ይታወሳል።

እነዚህ ወጣቶች በበዓሉ ድምቀት ሰረገላ በማዘጋጀት እና በማጓጓዝ ላይ እንዳሉ በኤሌክትሪክ ንኪኪ በተከሰተ አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ማህበረሰቡን በእጅጉ አሳዝኗል።

ይህ ክስተት የወጣቶቹን ቤተሰቦች ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል። በተለይም፦

ከሟቾች መካከል የአቶ አበበ ተፈራ ባለቤት የ9 ወር ነፍሰ ጡር መሆናቸውና ልጆቻቸውም አሁን ካሉበት ቤት በኪራይ ምክንያት እንዲወጡ መደረጋቸው፤

የሟች አቶ ፍቃዱ ተክለየስ ቤተሰቦች የሚመገቡት የሌላቸው 5 ቤተሰቦች በችግር ላይ መውደቃቸው፤

ሌላኛው ሟች አቶ ሄሮጳ ማሞ የቤተሰቡ አስተዳዳሪና ብቸኛ ደጋፊ በመሆኑ ቤተሰቡ በከፍተኛ ሃዘንና ችግር ውስጥ መገኘቱ ሁኔታውን ይበልጥ አሳዛኝ ያደርገዋል።

ስለሆነም እነዚህን የተቸገሩ ቤተሰቦች ለመርዳት ከጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።

ለተጎጂ ቤተሰቦች ተብሎ በተከፈተው የጋራ የባንክ አካውንት ድጋፍዎን ማድረግ ይችላሉ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ አቢሲኒያ ባንክ፦

ማክሰኞ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሚደረገው የቀጥታ ስርጭት ላይ በመሳተፍና ይህን መልዕክት ለሌሎች በማጋራት የድርሻዎን እንዲወጡ በትህትና እንጠይቃለን።

ፈጣሪ ለሟቾች መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...