አጋፋሪ ነበርኩ

Date:


የብርቱካንን “መመለስ” በፈረንሳይ ለጋሲዮን መረቅነው፦ በግራሞት ጭምር።

ብርቱካን፣ በ1992 ዓም የምርጫ ቅስቀሳ ባደረገችበት፣ ነሐሴ 20 ቀን 1999 ዓም መኪና በተሸለመችበት በፈረንሳይ ለጋሲዮይ ልበ ብርሃን ቅን ልቦና አዳራሽ፣ ዛሬ ሶስተኛውን ዝግጅት አከናወነች፦ “መመለስን” አስመረቀችበት። እና በፈረንሳይ ለጋሲዮን የምርቃቱ ታዳሚ ዘንድ ግራሞትም ሆነ።

የብርቱካንን መፅሐፍ ለመመረቅ ወደ አዳራሹ የመጣው ነዋሪ የተገረመው ያለ ምክንያት አልነበረም።
ወደ አዳራሽ ሲገባ መፅሐፉን ለመግዛት ጠየቀ።
“100 ብር” ተባለ።
እየተገረመ መፅሐፉን በመቶ ብር ሒሳብ ይዞ ወደ አዳራሹ ገባ።
እኔ ግን አልገረመኝም።

ይህ የምረቃ ፕሮግራም ሲዘጋጅ በአስተባባሪነት አብሬአት ነበርኩ።
“ወሰን እኔ የፈረንሳይ ሕዝብ መፅሐፌን እንዲገዛ አላስጨንቀውም፤ ምክንያቱም የራሱ ታሪክ ነው። ብችል በነፃ፣ ካልሆነ በቅናሽ ዋጋ ነው ለሕዝቡ የምሰጠው” አለችኝ።
እንዳለችውም አደረገች።
ለምረቃ ለመጣው ታዳሚ ሁሉ በመቶ ብር መፅሐፏን አደለች።

ደስም አለኝ።

መውጫ

ዛሬ የፈረንሳይ ለጋሲዮኑን የ”መመለስ” መፅሐፍ ምርቃት መድረክ መሪ ነበርኩ፦ ዋና አጋፋሪ።
መድረክ መምራቱ የተዋጣልኝ ይመስለኛል።
እሪፍ ጊዜ ነበረን።
እናመሰግናለን የፈረንሳይ ልጆች።

ከጋዜጠኞ ወሰንሰገድ ገብረ ኪዳን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...