በሆንግ ኮንግ ታይ ፖ አውራጃ ውስጥ በሕዝብ መኖሪያ ቤቶች ላይ በደረሰ ከባድ የእሳት አደጋ ቢያንስ 55 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ እና ከ270 በላይ የሚሆኑት ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
ባለሥልጣናቱ እንዳሉት በእሳት ከተያያዙት ሰባት ሕንፃዎች ውስጥ አራቱን መቆጣጠር እንደተቻለ እና የቀረቱን ህንፃዎች ደግሞ እስከ ምሽት ድረስ ለማጥፋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
እሳቱ እየቀነሰ በመጣ ቁጥርም እሳቱ መጀመሪያ እንዴት ሊነሳ ቻለ? እና ተጠያቂው ማን መሆን አለበት? የሚሉ ጥያቄዎች እየተበራከቱ እንደመጡ ተነገሯል፡፡
እሳቱ በፍጥነት እንዲስፋፋ አድርገዋል ተብለው ከተጠረጠሩ ተቀጣጣይ ነገሮች ጋር በተያያዘም በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው ሦስት የግንባታ ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚዎች በፖሊስ መያዛቸው ተገልጿል፡፡
የእሳት አደጋ ሠራተኞች አሁንም እሳቱን ላማጥፋት ከፍተኛ ጥረት ይያደረጉ ይገኛሉ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
