“በረመዳን ወር የምንተገብራቸውን መልካም ዕሴቶች የሕይወታችን ልምዶች ልናደርጋቸው ይገባል”

Date:



በረመዳን ወር የምንተገብራቸው የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና መሰል መልካም እሴቶችን ሁልጊዜም የሕይወታችን ልምዶች ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ገለጹ፡፡

ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ረመዳን መሠረታዊ እሴት በሰዎች ልብ ውስጥ የፈጣሪ ፍራቻ፣ መተዛዘን፣ ስለሌሎች መኖርን፣ መደጋገፍንና ማሰብን የሕይወታችን አካል እንድናደርግ ለ11 ወራት የሚሆን ስንቅ የሚይዝበት ወር ነው።

በመሆኑም በረመዳን ወር የምንተገብራቸውን የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና ለሌሎች መልካም እሴቶች ሁልጊዜም የሕይወታችን ልምዶች አካል ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ረመዳን አንዱ ስለሌላው የሚኖርበት ስለሆነ መልካም ተግባራት በስፋት የሚከናወኑበት ወር መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ ተግባር ደግሞ ሰዎች ዘወትር ሊኖራቸው የሚገባ ባሕሪ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

እኛ ዋጋ ለማግኘት ብለን በፈቃዳችን ስንፆም ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን ማሰብና አለኝታነታችንን ማሳየት ይገባናል ብለዋል።

(ኢ ፕ ድ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...