በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 1 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ለዘር ዝግጁ ተደረገ

Date:

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለ2017/18 መኸር እርሻ እስካሁን 1 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ለዘር ዝግጁ መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ፈቃዱ ወዬሳ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት በመኸር እርሻ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር በላይ ማሣ በዘር ለመሸፈን ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

ዝግጅቱ ሜካናይዝድ እርሻን ጨምሮ እንደተከናወነ ገልጸው ከመኸር እርሻ 55 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

እስካሁን 1 ሚሊየን 20 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለዘር ዝግጁ ተደርጓል ያሉት ዳይሬክተሩ ማሽላ በቆሎ እና ሌሎች ሰብሎች እንደሚዘሩ አመልክተዋል።

አርሶ አደሩ ማሣውን ተስማሚ በሆኑ ሰብሎች በመሸፈን ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘርን ጨምሮ ሌሎች ግብዓቶችን በፍጥነት ለማሰራጨት በትብብር እየተሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...