በቻይና የሚገኝ አንድ ድርጅት 26 ሚሊዮን ዶላር ለሠራተኞቹ በቦነስ መልክ አከፋፈለ

Date:

በቻይና ሄናን ግዛት የሚገኘው ሄናን ኩዋንግሻን ክሬን የተሰኘው ድርጅት እና መሥራቹ ኩይ ፔጁን፣ ካገኙት 270 ሚሊዮን ዩዋን ትርፍ ውስጥ 180 ሚሊዮን ዩዋን (26 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) ለሠራተኞቻቸው በቦነስ መልክ በማከፋፈላቸው በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆነዋል።

እኤአ የካቲት 13 ቀን 2026 በተካሄደው ዓመታዊ የድርጅቱ በዓል ላይ ከ60 ሚሊዮን ዩዋን በላይ የሚሆን የጥሬ ገንዘብ ኖት በረዣዥም ጠረጴዛዎች ላይ ተደርድሮ የቀረበ ሲሆን፣ ሠራተኞች በተዘጋጀ የገንዘብ መቁጠር ውድድር ላይ በተሰጣቸው የተወሰነ ጊዜ ውስጥ የቆጠሩትን ያህል ገንዘብ በሙሉ በነፃ ይዘው እንዲሄዱ ተፈቅዶላቸዋል።

የድርጅቱ ባለቤት ከዚህ ቀደም ይሰጡ የነበሩ እንደ ማጠቢያ ማሽንና የወርቅ ጌጣጌጦችን በመተው ለእያንዳንዱ ሰው ተጨማሪ 20,000 ዩዋን የጥሬ ገንዘብ ስጦታ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን፣ ድርጊቱንም የፈጸሙት የሠራተኞቻቸውን የዕለት ተዕለት የኢኮኖሚ ችግር በሚገባ ስለሚረዱ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ያልተለመደ የቦነስ ክፍያ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ትልቅ አድናቆትንና ቅናትን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ ብዙዎች ድርጅቱን ለሠራተኞቹ ባሳየው አሳቢነት እያመሰገኑት ይገኛሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ...

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...