በተዋናይት ደራሲና ፕሮዲዩሰር ቅድስ ባየልኝ ተጽፎ የተዘጋጀው “ሊያ” ፊልም ሊመረቅ ነው፡፡
በፊልሙ ላይ ተወዳጅና አንጋፋ የሆኑት ተዋናይ ወለላ አሰፋ፣ ግሩም ኤርሚያስ፤ ቅድስት ባየልኝ፣ ዲጄ ሉና እና ሌሎች እንደተሳተፉበት ተገልጿል።
የኢትዮ ውድ ኢንተርቴይመንት የኢትዮጵያ ተወካይ የፊልሙ ረዳት ዳይሬክተር ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሶስት አመት የፈጀ መሆኑን እና በወጪ ደረጃ ከ35 ሺ በላይ የአሜሪካን ዶላር መፍጀቱን ገልጿል።
ፊልሙ የፊታችን ሀምሌ 10/2017 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በአለም ሲኒማ በታላቅ ድምቀት እንደሚመረቅ ሀምሌ 3/2017 ዓ/ም በግዮን ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተነግሯል፡፡
ፊልሙን በመጻፍ እና በማዘጋጀት የተሳተፈችው ቅድስ ባየልኝ ከዚህ ቀደም ህይወት እንደዋዛ፣ እጸበለስና ከአትላንቲክ ባሻገር የተሰኙ ፊልሞችን በመድረስ፣ በመተወንና በማዘጋጀት ተሳትፎ ማድረጓ ይታወሳል፡፡
