በአዲስ አበባ ከተማ ጨለማን ተገንበማድረግ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች ምቹ ናቸው ተብለው በተለዩ አካባቢዎች የደህንነት ስጋትን የሚቀንስ የመብራት አገልግሎት እንዲያገኙእየተደረገ ነው ተባለ

Date:

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ለህይወትና
ለንብረት ስጋት በሆኑ 242 ሺህ 179 ጨለማ የሚበረታባቸው ቦታዎች መብራት ማስገባቱን አስታውቋል።

አካባቢዎቹ ድቅድቅ ጨለማ የነበሩ በመሆናቸው ለዝርፊያ፣ ጉዳት ለማድረስናሕይወትን ለማጥፋት ምቹ እንደነበሩ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ ገብሬ ዳኘው ለአራዳ ገልጸዋል።

ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ራሱን የቻለ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሲሰራ ቆይቷል ያሉት አማካሪው፥ መብራቶቹ መሰራታቸው የመፍትሄው አንድ አካል መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ወደ 72 ሺህ 378 በሚሆኑ ጨለማ ቦታዎች ላይ መብራት ለማስገባትዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል።

እንዲሁም ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት በሆኑ አራት ቦታዎች ላይ የፖሊስ ማዕከላት መሰራታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም እንደነዚህ አይነት ስጋት ያለባቸውን ቦታዎች በመለየት ወንጀልንየመከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።

aradaFm

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አደይ ኢትዮጵያ ጓል አስመራ…!!

የቀድሞ ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የስንብት ቃል ለጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ...

ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሁለተኛው ዙር ድርድር ሊደረግ እንደሚችል ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር...

በ”ፊንቴክ” ኢንቨስትመንት በተጠረጠሩት ላይ ተጨማሪ ጊዜ ተፈቀደለት

ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን ለምርመራ እንዲፈቀድለት ባለፈው አርብ በነበረው...

ክፍሌ አቦቸር እና ‹‹ይህ ነው ምኞቴ…››

ሠሎሞን ለማ ገመቹ ግዮን መጽሔት :- ሻለቃ ከፍሌ አቦቸር ስለ...