በኢትዮጵያ የመነጽር ጥራት ቁጥጥር እጦት ለከፋ የዓይን ችግር እያጋለጠ ነው

Date:

በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ደረጃ የመነጽርን ጥራት እና ደረጃ የሚቆጣጠር አካል አለመኖሩን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስታውቋል ። በዚህም የተነሳ ዜጎች ጥራቱ የተረጋገጠ መነጽር ስለማያገኙ ለከፋ የዓይን ጤና ህመም እየተጋለጡ መሆኑን ተጠቁሟል።

የኮሌጁ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ሳዲቅ ታጁ እንደተናገሩት፣ መነጽር በዓይን ጤና ውስጥ እንደ መድሃኒት የሚያገለግል የህክምና ቁስ ቢሆንም፣ ጥራቱንና ደረጃውን የሚለይለት እና የሚቆጣጠርለት አካል በሀገር አቀፍ ደረጃ የለም።

በዚህም ምክንያት ዜጎች ጥራቱ ያልተረጋገጠ ምርት በመግዛት ለተደጋጋሚ ወጪ እና ተጨማሪ የዓይን ችግር እየተጋለጡ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በተጨማሪም የመነጽር ጥራት ቁጥጥር ባለመኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የመነጽር ቤቶች እና በየመንገዱ መነጽር የሚያዞሩ ግለሰቦች በመብዛታቸው፣ እንዳሻቸው ሰርተውና ዋጋ ተምነው ለተጠቃሚው እያቀረቡ ነው ብለዋል። ይህ ደግሞ ብዙዎችን ለከፋ የዓይን ጤና ችግር እያጋለጠ ነዉ ሲል ኢፕድ ባለሞያውን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል ።

መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆግ መነጽር እንዴት መሰራቱና መገጣጠም እንዳለበት፣ የት ቦታ መሰራቱ እንዳለበት፣ በምን ያህል የጥራት ደረጃ መሰራቱ እንዳለበት፣ በምን አይነት መልኩ መሸጥ እንዳለበት የሚሉትን ጉዳዮች ለይቶ የሚሰራ አካል መመደብና አፈጻጸሙን መቆጣጠር ያስፈልጋል ተብሏል።

Source: capitalethiopia

ቀዳሚ ጽሑፍ
ቀጣይ ጥሑፍ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...