በከተማ አስተዳደሩ የሚገኝ የትኛውም መስሪያ ቤት የሆቴል ግዢ እንዳይፈጽም ተከለከለ

Date:


በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ሁሉም የከተማ አስተዳደር ቢሮዎች እና ከፍለ ከተሞች ለሆቴል ኪራይ መክፈል አይችሉም ሲሉ ነግረውናል፡፡ 

በከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ቢሮ ተፈርሞ ከወጣ ደብዳቤ ላይ እንደተመለከትነው በ2018 በጀት ዓመት ሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራቸውን ለመገምገምም ሆነ ለስልጣና ከበጀታው ላይ ለሆቴሎች እንዳይከፍሉ የሚከላክል ነው፡፡

መስሪያ ቤቶቹ ልዩ ልዩ ስብሰባዎችን፣ ስልጠና እና ግምገማዎችን ለማድረግ የመንግስት በየክፍለ ከተሞቻቸው የሚገኙ የመንግስት የመሰብሰቢያ አዳራሾችን እና ከፍቴሪያዎችን እንዲገለገሉ ያዛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት እቅድ መከወኛ 350.1 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን ያስታወሰው ቢሮው 70 በመቶ የሚሆነው ለካፒታል በጀት የተደለደለ መሆኑን አስታውሷል፡፡

ቀሪው ለመደበኛ ስራዎች መከወኛ መመደቡን ተናግው ይህን በጀት በእቅዱ መሰረት ስራ ላይ ለማዋል አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡

መስሪያ ቤቶቹም ይህን የተመደበላቸውን በጀት በቁጠባ እንዲጠቀሙም አሳስቧል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...