“በየሳምንቱ አንድ ሚሊዮን ዜጎችን እየመዘገብኩ ነው”

Date:

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ፅሕፈት ቤት በየሳምንቱ አንድ ሚሊዮን ዜጎችን እየመዘገበ መሆኑን በማብሰር፣ እስካሁን የተመዝጋቢዎች ቁጥር 37.5 ሚሊዮን መድረሱን አስታውቋል።

የፅሕፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ እንደገለጹት፤ እስከ መጪው ሰኔ ወር ድረስ ተመዝጋቢዎችን 90 ሚሊዮን ለማድረስ ግብ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል።

ይህ ዲጂታል መታወቂያ ለማንነት ማጭበርበር መከላከያነት ከመዋሉ ባለፈ፣ በሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (GDP) ላይ የ6 በመቶ እድገት እንደሚያስገኝ ይጠበቃል።

መታወቂያው ለባንክና ቴሌኮም አገልግሎቶች፣ ለግብር ከፋይ መለያ (TIN) እና ለተማሪዎች ምዝገባ እንደ ቅድመ-ሁኔታ የሚያገለግል ሲሆን፣ ስደተኞችም የሀገሪቱን አገልግሎቶች እንዲያገኙ ያስችላል።

ምንም እንኳን የክትትል ስጋት ያላቸው ወገኖች ቢኖሩም፣ ፕሮግራሙ ግልጽነትን በመፍጠር የመልካም አስተዳደርና የደህንነት ስራዎችን ለማቀላጠፍ ያለመ ነው።

ለዚህም ስኬታማነት የመገናኛ ብዙኃን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሚና ወሳኝ መሆኑ በፕሮግራሙ ላይ ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...