በደብረብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች የተቋረጠባቸዉ ድጋፍ ከወራት በኋላ ማግኘት መቻላቸዉን ገለጹ።
ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች በቂ ደጋፍ እየተደረገላቸው አለመሆኑን ሲያነሱ ቆይተዋል።
ከዚህ ቀደም ለሃገሬ ቴሌቭዥን በቦታው የሚገኙ ተፈናቃዮቹን በማናገር ዘገባዎች ወደ እናንተ አድርሶ ነበር ፡፡
ከተፈናቅሉ 5ኛ አመታቸዉ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ጣቢያችን ያናገራቸው አስተባባሪዎች የመንግስት አካል እስካሁን አነጋግሯቸው እንድማያዉቅ ገልጸዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ ከሶስት ወር በኃላ አሁን ላይ ድጋፍ እንደተደረገላቸዉ በመግለጽ ድጋፉን ላደረጉላቸዉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አሁንኑ ድጋፍ ካለው ችግር አንጻር በቂ አለመሆኑንና በሁለትና በሶስት ወራት አንዴ የሚደረገዉ ድጋፍ በየወሩ እንዲደረግላቸዉና በቋሚነት የሚቋቋሙበት መንገድ እንዲያመቻችላቸዉ ጠይቀዋል፡፡
(ሀገሬ ቴቪ)፤
