በጋዛ በረሃብና በተመጣጠነ ምግብ እጦት የ147 ሰዎችን ህይወት ተቀጥፏል

Date:


በጋዛ ቢያንስ 14 ፍልስጤማውያንና ሁለት ህፃናትን ጨምሮ በቅርቡ በረሃብና በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን የጤና ባለስልጣናት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል ።

ይህ አሳዛኝ ክስተት እስራኤል በጥቅምት 2023 ጦርነት ከጀመረች ወዲህ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሞቱት ሰዎች ቁጥርን ወደ 147 እንዲያድግ አድርጓል፤ ከእነዚህ ውስጥም  88ቱ ህፃናት መሆናቸው ነው የተነገረው ።

ይህ አስከፊ ዜና የወጣው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተከበበችው ጋዛ ግዛት “እውነተኛ ረሃብ” እየታየ መሆኑን ከገለጹ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ከሁለት ቀን በፊት ባወጣው መግለጫ፣ በጋዛ ውስጥ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምጣኔ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስጠንቅቋል። በተለይም በሐምሌ ወር ብቻ የሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ነው ያለው ድርጅቱ ።

ዩኒሴፍ በበኩሉ ባወጣው ሪፖርት፣ በጋዛ ያሉ ህፃናት “በረሃብ እየሞቱ” መሆናቸውን ገልጿል። ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሞቱ ህፃናት ቁጥርም ከ52 ወደ 80 ከፍ ብሏል። ይህም ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ54 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አልጄዚራ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...