በጨረቃ ላይ ለሚከናወን ግንባታ የሚያገለግል የቁፋሮ ማሽን ይፋ የተደረገ

Date:

አስትሮፖርት ስፔስ ቴክኖሎጂስ እና አስትሮላብ የተባሉ የኢንጂነሪንግ ስታርት አፕ ኩባንያዎች በጨረቃ ላይ ለሚከናወን ግንባታ ተብሎ የተሰራውን “UTIPA Excavator” የተሰኘ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራ የቁፋሮ ማሽን ሙከራ በስኬት ማጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል።

ይህ ወሳኝ የሆነ የማሳያ መርሃ-ግብር ባለፈው ጥር ወር በሳን አንቶኒዮ በሚገኘው የአስትሮፖርት ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ መከናወኑን የኩባንያዎቹ መግለጫዎች አመልክተዋል።

ይህ ዘመናዊ የቁፋሮ ማሽን በጨረቃ ላይ የግንባታ ቦታዎችን ለማዘጋጀት እና ከ “Astrolab’s FLEX” ሮቨር ጋር በመቀናጀት ሰው አልባ በሆነ መንገድ የተለያዩ ተግባራትን ለማከናወን የተቀረጸ ነው።

የጨረቃ ላይ ቁፋሮ እና የግንባታ መሣሪያዎችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች እንደሚገልጹት፣ በጨረቃ ላይ በብዛት ይገኛል ተብሎ የሚታሰበው “Helium-3” የተሰኘው የሂሊየም አይሶቶፕ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩ ለዚህ የጠፈር ላይ ግንባታና የሀብት ፍለጋ እንቅስቃሴ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ምክንያት ሆኗል።

የአስትሮፖርት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳም ዚሜኔስ እንደገለጹት፣ ይህ የቁፋሮ ማሽን ሙከራ ስኬታማ መሆን ቴክኖሎጂያቸው በንድፈ-ሐሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በተግባርም መሥራት የሚችል መሆኑን ያረጋገጠ ነው።

ይህ ግስጋሴ ወደፊት በጨረቃ ላይ ለሚገነቡ መሠረተ ልማቶችና ለጠፈር ምርምር አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥር መሆኑ ታምኖበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...