ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ50 ኩንታል በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ አደረገ

Date:



በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማዕድን ዘርፍ እየተተገበረ ባለው የሕግ ማሕቀፍ እና የክትትል ሥራ ባለፉት ሰባት ወራት ከ50 ኩንታል በላይ ወርቅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ናስር መሀመድ እንደገለፁት፤ በ2017 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 47 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደርጎ የነበረ ሲሆን፣ በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት ሰባት ወራት ብቻ የቀረበው የወርቅ መጠን የዓምናውን ጠቅላላ ዓመት የሚበልጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

ክልሉ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ 70 ኩንታል ወርቅ ለመሰብሰብ አቅዶ በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው ቀደም ሲል የነበሩ ሕገወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል አምራቾች እና አቅራቢዎች ሕጋዊ ፈቃድ ወስደው እንዲሠሩ በመደረጉና አቅራቢዎች ወርቅ ገዝተው በሕጋዊ መንገድ ወደ ባንክ የሚያስገቡበት የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋቱ ነው።

በተጨማሪም የክልሉ መንግሥት እና የጸጥታ አካላት በቅንጅት በመሥራት “የክልሉን ሰላም ማስጠበቃቸው” ወርቅ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለባንክ እንዲገባ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። (ኢፕድ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...