ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ የእስር ማዘዣ አወጣች።
ወደ ጋዛ ሰብአዊ እርዳታ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ መርከብ በእስራኤል በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ ጋር በተያያዘ በሚደረግ ምርመራ ምክንያት የእስር ማዘዣው እንደወጣ ተገልጿል።
የቱርክ የፍትሕ ሚኒስትር አኪን ጉርሌክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ መውጣቱን በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል።
ከአራት ወራት በፊት ከ40 አገራት የተውጣጡ ከ430 በላይ የፍልስጤም የመብት ተሟጋቾች በእስራኤል ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል።
የመብት ተሟጋቾቹ በመርከብ ወደ ጋዛ ሰብአዊ እርዳታ ይዘው እየተጓዙ ነበር።
ጋዛ ላይ የተጣለውን ዕቀባ የሚቃወም ንቅናቄ አባል የሆኑት የመብት ተሟጋቾቹ በቱርክ አውሮፕላኖች ከእስራኤል ወደ ቱርክ ተወስደዋል።
ቱርክ ከዚህ ቀደምም በኔታንያሁ እና ሌሎችም ባለሥልጣናት ላይ የእስር ማዘዣ አውጥታለች።
ይህም እስራኤል በጋዛ ከምትፈጽመው ድርጊት ጋር በተያያዘ “በዘር ጭፍጨፋ” ክሶች ምክንያት የወጣ የእስር ማዘዣ ነው።
