“ታሪኩ እንዳይጻፍ ግዝት የጣለው የልብ ሐኪም”

Date:

ዛሬ 81ኛ የልደት ቀኑ ነው

ደጋግሞ
“ይቺን ሠራ ብላችሁ አታሳንሱኝ”
“የምችለውን ሠራሁ ሞከርኩ እንጂ ያሰብኩትን ያህል አልሠራሁም።”
“ማድረግ ከሚገባኝ ውጭ አንዳችም የሚያስጨበጭብ፣ መጽሐፍ የሚያስጽፍ፣ ዲስኩር የሚያስነግር ገድል የለኝምና ተውኝ!” የሚለው፤

ስለሥራው፣ ስለታሪኩ፣ ፈፅሞ ሊነገርለት የማይሻው፣ የህይወት ታሪኩን እንዳንጽፍ በሰው መሐል የግዝት ያህል እግድና ጥብቅ ክልከላ የጣለብን ሐኪም ልደቱ ዛሬ ነው!

እኔ ለአደባባይ ትሕትና ሳልገዛ፤
ራስን አሳልፎ መስጠት!
ያሰቡትን ባሰቡት ልክ መጨረስ!
ለሀገርና ወገን ዘመንን መስጠት!
ከታይታና የእውቅና ሽሚያ መራቅ!
የአዕምሮ-ውልዱን His Brain Child “እኔ እዚህ አድርሻለሁ በቃኝ!… እናንተ ቀጥሉ!” ብሎ ኮሽ ሳይልበት ለትውልድ የማስተላለፍ ከፍ ያለ ሰብዕና ባለቤት የሆነ ማነው ብትሉኝ በሙሉ ልብና መተማመን፤

“ይህ ሰው በዕንባው ሀገር ያከመ ታላቅ ኢትዮጵያዊ የልብ ሐኪም #ዶርበላይአበጋዝ ነው እላችኋለሁ!

ለአደባባይ ትሕትና

እኒህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሐኪምና በጎ አድራጊ፣ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማህበርና የልብ ማዕከል በኢትዮጵያ መሥራች፣ ይህችን ምድር በጎ ሊሠሩባት ከተቀላቀሉ እነሆ ህዳር 12 ቀን 2018 አ.ም #81_አመት ሆኗቸዋል!!

ዶ/ር በላይ፤ ታላቅ ክብር፣ ታላቅ ፍቅር፣ የሚገባቸው የሀገር ባለውለታ ኢትዮጵያዊ ናቸውና ሞቅ ባለ ስሜትና አክብሮት እንኳንም ተወለዱልን በማለት መልካሙን እንመኝላቸው ዘንድ እለምናችኋለሁ!

እኔ በግሌ እሳቸውን በተመለከተ፤ ላነሳውና ላሳካው የምሻውን ዐብይ ጉዳይ በቅርቡ ይፋ አደርጋለሁና አብራችሁኝ ትቆሙ ዘንድ ከወዲሁ የአክብሮት አደራየን አስቀድማለሁ! የልብ አዳኛችን #ዶክተርበላይ_አበጋዝ እንኳንም_ተወለዱልን!!

ረዥም ዕድሜና ሙሉ ጤና እንመኝልዎታለን! ተስፋዬ ማሞ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...