ታዋቂው ሳይንቲስት አመሃ በላይ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

Date:

በማይክሮ አልጌ ባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ምሁር የነበሩት አመሃ በላይ (ዶ/ር) በተወለዱ በ79 ዓመታቸው፣ የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ዶ/ር አመሃ የቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ሲሆኑ፣ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ ከዩናይትድ ኪንግደም አግኝተዋል።

ወደ ሀገራቸው በመመለስም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ13 ዓመታት በመምህርነትና በባዮሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊነት አገልግለዋል።

በሙያ ሕይወታቸው ከፍተኛ ዝና ያተረፉት፣ በካሊፎርኒያው “Earthrise Nutritionals” ተቋም ውስጥ ለ26 ዓመታት በከፍተኛ የቴክኖሎጂ መኮንንነት (CTO) በሰሩበት ወቅት ነው።

በዘርፉ ባላቸው ጥልቅ ዕውቀትና ለስፒሩሊና ኢንዱስትሪ ባበረከቱት አስተዋጽኦም “ሚስተር ስፒሩሊና” (Mr. Spirulina) የሚል ስያሜ እስከማግኘት ደርሰዋል።

ዶ/ር አመሃ በላይ ከዓለም አቀፍ ሥራቸው ባሻገር፣ ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ባላቸው ጥልቅ ፍቅር ይታወቃሉ። የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ እና ዘላቂ ልማት ምክር ቤት መሥራች በመሆንም አገልግለዋል።

በተለይም በጣና ሐይቅ፣ በአባያ ሐይቅና በአዋሽ ወንዝ ላይ የተከሰተውን አደገኛ የእንቦጭ አረም ለመከላከል በሚደረገው ሳይንሳዊ ጥረት ውስጥ በንቃት ተሳትፈዋል።

የዶ/ር አመሃ በላይ የቀብር ሥርዓት ቅዳሜ፣ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈጸም ታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...