ትራምፕ የቲክቶክ የሽያጭ ስምምነት ከእግዱ በፊት እንደሚፈረም ገለጹ

Date:




ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቻይናው ባይት ዳንስ የቲክቶክን ድርሻ እንዲሸጥ ከኩባንያው ጋር የተጀመረው ድርድር መተግበሪያው ከፊታችን ቅዳሜ በኋላ በሀገረ አሜሪካ ከመታገዱ በፊት በስምምነት ፊርማ እንደሚጠናቀቅ አመላክተዋል።

ትራምፕ ቲክቶክ ቻይናዊ ያልሆነ ገዢ እንዲያፈላልግ እስከ ቅዳሜ ኤፕረል 5 ቀን ቀነ-ገደብ አስቀምጠዋል። ይህ ካልሆነ ግን ከብሔራዊ ደህንነት ጋር በተያያዘ መተግበሪያው በሀገረ አሜሪካ እገዳ እንደሚጣልበት አስጠንቅቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ እሁድ ዕለት ጉዳዩን ለጋዜጠኞች ሲያብራሩ፥ “አቅሙ ያላቸው በርካታ ገዢዎች አሉን፣ ለቲክቶክ ከፍተኛ ፍላጎት አለ፤ ቲክቶክ በአሜሪካ ሕያው ሆኖ መቀጠሉን ማየት እፈልጋለሁ” ብለዋል።

170 ሚሊዮን አሜሪካውያን የሚጠቀሙበት የአጭር ቪዲዮ መተግበሪያ የቲክቶክ የድርሻ ሽያጭ ስምምነት እንዲሳካ ቻይና ለምትጫወተው ሚና እንደ ማበረታቻ የታሪፍ ቅናሽ ሊያደርጉላት እንደሚችሉም ተናግረዋል።

https://t.me/EBCNEWSNOW

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...