ቻይና የሱማሊላንድን መገንጠል አልደግፍም ስትል አስታወቀች

Date:

ቻይና ሱማሊላንድ እና ታይዋን እያደረጉት ያሉትን ግንኙነት በፅኑ ተችታለች።

ከቅርብ ግዜያት ወዲህ ተገንጣይ አገራቱ ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ በተለያየ መንገድ ሲገልፁ ነበር።

ይሁንና በሱማሊያ የቻይና አምባሳደር የሆኑት ዋንግ ዩ ፤ ግንኙነታቸውን ተገንጣይነትን ለማስተዋወቅ የተጠነሰሰ ብለውታል።

‹‹በአለም ላይ ያለው አንድ ቻይና ነው፡፡ ታይዋንም የቻይና አንድ አካል ናት፡፡ በርካታ አገራት የቻይናን አንድነት ይደግፋሉ›› ያሉት አምባሳደሩ መሠረታዊው እውነትም ይሄ ነው ብለዋል።

አክለውም የሱማሊያን ሉአላዊ አንድነት ለማስጠበቅ የቤጂንግ መንግስት ከሱማሊያ ፌዴራል መንግስት ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ ነው የገለፁት ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...